የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ተወያዩ።
==========================
<<የመሃሉ ዘመን!>>በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ የተወያዩ ሲሆን የውይይቱ ዋንኛ አላማም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ተከታታይ 7 አመታት ለውጡን ለማፅናት በተደረጉ ጥረቶች፣ የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ውስጣዊ፣ ቀጠናዊና አለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲሁም አሁናዊ ሀገራዊ ሁኔታና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከት የቢሮው ሰራተኞችና አመራሮች የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በቀጣይም እንደሀገር ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችን በሚገባ መቀልበስ የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ መሆኑን በመግለፅ ሁሉም አመራር እና ሰራተኛ በተለይ በአገልግሎት ዘርፍ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ በመረባረብ የተጀመረውን ለውጥ በማፅናት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይር ሀጂኑር መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ <<የመሃሉ ዘመን!>>በሚል መሪ ቃል ለውይይት መነሻነት የሚሆን ሰነድ በድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ለገሰ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የቢሮው አመራሮች እና ሠራተኞች ወቅታዊ ሀገራዊ ፣ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ወቅታዊ የሆነ መረጃ ሊኖራቸው እንደሚገባና በዚህም ሀገራዊ ለውጡን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር እያደረግን ያለነውን ጥረት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ማናቸውንም ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ኃይሎችን በመጋፈጥ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንዲወጡም የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሰቦ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።